በደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ አማራዎች ሞትና የሴቶች እገታ እንደቀጠለ ነው።

ቤተሰቦቻቸው “የመንግስት ያለህ” ይላሉ!

(በአማራ ዜና አርታኢ)

ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ለውጥ አለ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ በሃገሪቱ የትምህርት ተቋማት አካባቢ የሚታየው ቀውስ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታዲያ፤ በኦሮምያ ክልል በወለጋ ዞኖች የሚታየውን ሰላም መደፍረስ ተከትሎ የትምህርት ተቋማት ላይ ትኩረት ያደረገና አማራውን ለጥቃት ያጋለጠ ስርዐት አልበኝነት ታይቷል። ይህም ጥቃት በተለይም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የከፋ እንደሆነ እየታየ ነው። ከአንድ ውር በፊት ተምሬ ቤተሰቤንና ሃገሬን እጠቅማለሁ ያለ የወልድያ አማራ ተማሪ መገደሉ ይታወሳል።  ይህ በቄሮ የሚታገዝ ቅጥ ያጣ የአመጸኛው የኦነግ ሸኔ  ተግባር አሁንም ቀጥሎ 16 የአማራ ሴቶች እንዲሁም የተወሰኑ ወንድ ተማሪወች  እንደታገቱ ተሰምቷል።

መንግስት ይህን መረን የለቀቀ ችግር ለመፍታት በሚል በወለጋ አካባቢ ወታደራዊ ስምሪት ቢያካሂድም፤ አካባቢውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ግን ከባድ ሆኖበታል። የታገቱ ተማሪዎችምDembi Dolo University እስካሁን ድረስ ነጻ ሊሆኑ አልቻሉም። ይህን ዘገባ እስካዘጋጀንበት ጊዜ ድረስ እንደቃረምናቸው ወሬዎችም ወደ ወለጋ መጓዝም ሆነ ከወለጋ መውጣት እንደማይቻል ለመረዳት ችለናል።

ልጆቻቸው በነዚህ በኦሮሞ ቄሮ በሚታገዙ ሃይሎች የታገቱባቸው በተሰቦችም በከፍተኛ ጭንቅ ላይ ናቸው። ልጆቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ለማዎቅ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙ ቤተሰቦችም በመንግስት ላይ ያላቸው እምነት እንደተመናመነ ይገልጻሉ። የመንግስት ያለህም ሲሉ ይደመጣሉ።

 

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s