የበረከት ስምዖን መጨረሻ?

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ግለሰቦቹ በጥረት ኮርፖሬት ፈጽመዋል ተብሎ በተጠረጠሩበት የሀብት ብክነት ወንጀል አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ)ን በጥረት ኮርፖሬት ከደረሰ የሀብት ብክነት ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ገልጿል።

የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ዝግአለ ገበየሁ ዛሬ ረፋድ ላይ ጉዳዩን በተመለከተ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ወደ ባህር ዳር መወሰዳቸውን አስታውቀዋል።

የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈፀመውም በክልሉ በመሆኑ ጉዳያቸው በክልሉ ፍርድ ቤት እንደሚታይም ነው ኮሚሽነሩ ያስታወቁት።

ኮሚሽኑ በእስካሁኑ ሂደት በግለሰቦቹ ላይ ክስ ለመመስረት የሚያስችለኝን ከበቂ በላይ ማስረጃ ሰብስቢያለሁም ብሏል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s