አንቶኒዮ ጉተሬስ የአለም ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ለተከሰተው የድርቅ አደጋ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ አቀረቡ:: ኢሳት (ጥር 23 ፥ 2009)

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሪስ የአለም አቀፉ ማህበረስብ በኢትዮጵያ እየተባባሰ ለመጣው የድርቅ አደጋ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪን አቀረቡ።

በአዲስ አበባ የሚገኙት የድርጅቱ አዲስ ዋና ጸሃፊ ጉተሬስ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ በኢትይዕጵያ በአዲስ መልክ ለተከሰተው የድርቅ አደጋ ሰብዓዊነት የተሞላበት ድጋፍ እንዲያቀርቡ ማሳሰባቸውን ፋይናንሻል ኢንተርናሽናል የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል።

አጋርነትን ማሳየት እንዳልገሳ ሊቆጠር አይገባም ያሉት ዋና ጸሃፊው ለድርቁ እንዲደረግ የቀረበው ድጋፍ ከፍትህና የራስን ጥቅም የማስጠበቅ ጉዳይ ተደርጎ መታየት እንዳለበት አክለው አስታውቀዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኦሮሚያ፣ ሶማሊ፣ አፋርና ደቡብ ክልሎች ስር በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች በተከሰተው አዲስ የድርቅ አደጋ 5.6 ሚሊዮን ሰዎች ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ መጋለጣቸውን በተደጋጋጋሚ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

የድርቁ አደጋ እየተባባሰ በመሄድ ላይ መሆኑን የገለጸው ተመድ፣ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አፋጣኝ ምላሽ እንዲደረግ በድጋሚ አሳስቧል።

በተለይ በአፋርና በሶማሌ ክልል ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች ቁጥር በመቸመር ላይ ሲሆን ፣ የአለም አቀፍ ድርጅቶች አስቸኳይ ካላደረጉ በሰው ህይወት ላይ የከፋ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።

በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ትምህርት ካቋረጡ ህጻናት በተጨማሪ ለውሃና ምግፍ ፍለጋ መንደራቸውን እየለቀቁ የሚሄዱ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ቁጥርም እየተበራከተ መምጣቱ ተመልክቷል።

መንግስት በበኩሉ ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ህጻናት ቁጥር ለመቀነስ አንድ ሚሊዮን አካባቢ  ለሚሆኑ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች የምግብ ድጋፍ እንዲቀርብላቸው ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።

በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ትምህርት ካቋረጡ ህጻናት በተጨማሪ ለውሃና ምግብ ፍለጋ መንደራቸውን እየለቀቁ የሚሄዱ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ቁጥርም እየተበክራከተ መምጣቱ ተመልክቷል።

መንግስት በበኩሉ ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ህጻናት ቁጥር ለመቀነስ አንድ ሚሊዮን አካባቢ ለሚሆኑ ተማሪዎች በትምህር ቤቶች የምግብ ድጋፍ እንዲቀርብላቸው ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል። እስከተያዘው አመት መጨረሻ ድረስ ይዘልቃል የተባለውን ይህንኑ የድቅ አደጋ ለመከላከል ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር አካባቢ እንደሚያስፈልግም መደረጉ ይታወሳል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s