የአማራ ሐኪሞች ማህበር ፕሬዚዳንት ከባህርዳር ከታፈነ ከ3 ቀናት በኋላ የት እንደታሰረ ታወቀ

(ዘ-ሐበሻ) የአማራ ሃኪሞች ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን እያገለገለ የነበረው ወጣቱ ዶክተር ጋሹ ግንዱ በባህህር ዳር ከተማ በስርዓቱ ወታደሮች ከተያዘ በኋላ ወደ የት እንደሰወሩት ሳይታወቅ የቆየ ሲሆን ከ3 ቀናት በኋላ ባህርዳር 09 ፖሊስ ጣቢያ እስር ቤት ታስሮ እንደሚገኝ ታወቀ::

አክቲቭስት ለገሰ ወልደሃና ካሰራጨው መረጃ ለመረዳት እንደተቻለው ዶ/ር ጋሹ በስርዓቱ ወታደሮች የታፈነው ባለፈው ሃሙስ ታህሳስ 27 ነበር:: ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ የታፈነው ዶ/ር ጋሹ ለ3 ቀናት የት ታፍኖ እንደተወሰደ ሳይታወቅ ቤተሰብ እና ጓደኞቹን ሲያስጨንቅ ነበር::

አማራ መሆን ወንጀል በሆነባት ኢትዮጵያ በጎጃም ክፍለሀገር በቡሬ አጠቃላይ ሆስፒታል በሜዲካል ዳይሬክተርነት ሲያገለግል የቆየው ዶ/ር ጋሹ በ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየፈጸመበት መሆኑንም ምንጮች ዘግበዋል::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s