የአባይ ተፋሰስ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ተፋሰሶች የላቀ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ ያለው ልዩ ቦታ በመሆኑ በርካታ ጥናቶች ተደርገውበታል:: የመጀመርያው የአባይና ጣና ዳሰሳ ጥናት የተካሄደው በእንግሊዞች ነበር:: ቀጣዩ ዝርዝርና ጥልቅ ጥናት የተካሄደው በአጼ ኃይለሥላሴ ልዩ ጥያቄ ሲሆን ምክንያቱም አወዛጋቢው የእንግሊዝና ጣልያን በ1925 ዓ.ም የተፈራረሙት ውል ነበር:: ይህ የወራሪ ሃይሎች ውል ጣልያን ኤርትራ የሚገኘውን ቅኝ ግዛቷንና ሶማሌ ያለውን ቅኝ ግዛቷን ለማገናኘት በኢትዮጵያ ላይ የባቡር ሀዲድ ግንባታ እንድትሰራ የሚፈቅድ ሲሆን እንግሊዝ ደግሞ በበኩሏ ጣና ኃይቅ ላይ ግድብ ገድባ ውሃውን በወቅቱ ቅኝ ግዛቷ ወደነበረችው ሱዳን እንድትልክ የሚያደርጋት ነበር ::
For more: