የልዩ ኃይል አመራርና ከወያኔ ኮማንድ ፖስቶች የአንዱ አዛዥ የነበረው ኮማንደር ዋኘው አዘዘው በስሩ የነበሩ ወታደሮችን ይዞ የአማራ ተጋድሎ አርበኞችን ተቀላቀለ

(ዘ-ሐበሻ) የትግራዩ ነጻ አውጪ መንግስት በየከተማው ያደራጃቸው የልዩ ኃይል አመራሮች እና የኮማንድ ፖስት አባላት በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች እየተፍረከረኩ እንደሚገኙ ተሰማ:: በኦሮሚያ በተለይም በአወዳይ አካባቢ የኮማንድ ፖስቱና የልዩ ኃይል አባላት በአካባቢው ታጣቂዎች በየቀኑ እርምጃ እየተወሰደባቸው ሲሆን በአማራ ክልል ደግሞ የኮማንድ ፖስት አዛዦች ሊከዱ ይችላሉ በሚል የቁም እስረኛ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመልክቷል::

እንደመረጃው ከሆነ የአማራ ክልል የልዩ ኃይል አመራርና ከወያኔ ኮማንድ ፖስቶች የአንዱ አዛዥ የነበረው ኮማንደር ዋኘው አዘዘው በስሩ የነበሩ ወታደሮችን ይዞ የአማራ ተጋድሎ አርበኞችን መቀላቀሉን ተከትሎ የሕወሓት መንግስት በከፍተኛ ብርክ ውስጥ እንደወደቀ የውስጥ ምንጮች አስታውቀዋል::

ወደ ሕዝቤ አልተኩስም በሚል ከአማራ ተጋድሎ ገበሬዎች ጋር የተቀላቀለው ኮማንደር ዋኘው አዘዘውና በስሩ ያሉ ወታደሮች የሕወሓት መንግስት ራስ ምታት የሆኑበት ሲሆን ሌሎች የኮማንድ ፖስቱ አዛዦችም ሊጠፉ ይችላሉ በሚል እንዲታሰሩ ት ዕዛዝ መውረዱን የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስታውቋል::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s