ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአውሮፓ አዲስ አበባ ሲገቡ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታወቀ ኢሳት (ህዳር 21 ፥ 2009)

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ፕሬዚደንት ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአውሮፓ አዲስ አበባ ሲገቡ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታወቀ።

የአይን ምስክሮች እንደገለጹት ዶ/ር መረራ ጉዲና በቁጥጥር ስር የዋሉት በምን እንደሆነ የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ የህወሃት መገናኛ ብዙሃን ዶር መረራ እንዲታሰሩ ሰሞኑን በቅስቀሳ ላይ እንደነበሩ ታውቋል።

በአውሮፓ ህብረት ግብዣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ምስክርነት ለመስጠት ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ከአትሌት ፈይሳ ለሊሳ ጋር ብራሰልስ የተገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ጥሰዋል የሚል ቅስቀሳ ሲደረግባቸው ቆይቷል። ለዚህም ይቀርብ የነበረው ምክንያት ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር በአንድ መድረክ መገናኘታቸውና ጎን ለጎን መቀመጣቸው መሆኑን መረዳት ተችሏል።

ዶ/ር መረራ ጉዲና አውሮፓ የተጋበዙትም በአንድ መድረክ የተገኙትም በአውሮፓ ፓርላማ ግብዣ ሆኖ ሳለ፣ በጉዳዩ ተጠያቂ መደረጋቸውና በዚህም መወንጀላቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

ዶ/ር መረራ ጉዲናን የያዟቸው ወገኖች ወዴት እንደወሰዷቸው ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የታወቀ ነገር የለም። ዶ/ር መረራ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት ምስክርነት መንግስትን አለማስደሰቱን ለማወቅ ተችሏል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s