በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሳይንስ ተማሪዎች ከአንደኛ እስከ አራተኛ አመት በሙሉ ታስረዋል

(ECADF) — የጎንደር ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ከብአዴን ባለስልጣኖች ጋር በመተባበር  ከአንደኛ አመት እስከ አራተኛ አመት ያሉትን የእንስሳት ሳይንስ ተማሪዎችን ሙሉ በሙሉ እስርቤት አስገብተዋቸዋል። ተማሪዎቹ የታሰሩበት ምክንያት በመማር ላይ ያሉት የእንስሳት ሳይንስ ትምህርት በኢትዮጵያ እምብዛም የሚታወቅ ባለመሆኑ እና ቀደም ሲል ተመሳሳይ ትምህርት ወስደው የተመረቁ ተማሪዎች ስራ ማግኘት ባለመቻላቸው የትምህርቱ አይነት እንዲቀየርላቸው ጥያቄ በማቅረባቸው ነው። ተማሪዎቹ ያቀረቡት ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጋር እየተከራከሩ በመክረማቸው ትምህርት ሊጀምሩ አልቻሉም ነበር። ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ዛሬ የዩኒቨርሲቲውን ግቢ እንዲለቁ የሚያሳስብ ማስታወቂያ ስተለጠፈባቸው ዩኒቨርሲቲው መልቀቂያ እንዲሰጣቸው ለመወያየት ከተሰበሰቡበት ቦታ ሁሉንም ወደ ፖሊስ ጣብያ ወስደዋቸዋል። የተወሰኑት ተማሪዎች በስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ ታስረው የሚገኙ ሲሆን የቀሩት ደግሞ በሁለተኛ ፖሊስ ጣብያ ታስረው ይገኛሉ። በተጨማሪም ባጋጣሚ እቦታው ተገኝታ የነበረች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተማሪም መታሰሯ ታውቋል። የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የታሳሪ ተማሪዎች ቤተሰቦች ሁኔታውን አውቀው ስለ ልጆቻቸው እንዲጠይቁ አሳስበዋል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s